Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል 686 ሺህ ሄክታር በአኩሪ አተርና ሰሊጥ እየለማ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 12 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል በተያዘው የምርት ዘመን 686 ሺህ 376 ሄክታር መሬት በአኩሪ አተርና ሰሊጥ ሰብል እየለማ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።

ለኢንዱስትሪ ግብዓትና የውጭ ምንዛሬ በሚያስገኙ ሰብሎች የተሻለ ምርት ለማግኘት ግብ ተይዞ እየተሰራ መሆኑ ቢሮው ገልጿል።

በዚህም ለሀገሪቱ የውጭ ምንዛሬ በሚያስገኘው የሰሊጥ ሰብል 340 ሺህ ሄክታር መሬት ለማልማት ታቅዶ 446 ሺህ 263 ሄክታር መሬት ማልማት መቻሉ ተመላክቷል፡፡

ይህም ከዕቅዱ በ106 ሺህ 263 ሄክታር ብልጫ እንዳለው በቢሮው የሰብል ልማትና ጥበቃ ዳይሬክተር አቶ አግደው ሞላ ተናግረዋል፡፡

ቀሪው መሬት በአኩሪ አተር ሰብል የለማ መሆኑን ጠቁመው÷በሁለቱ ሰብሎች እየለማ ካለው መሬት ከ11 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት እንደሚጠበቅ ጠቁመዋል፡፡

በዕቅድ የተያዘው ምርት እንዲገኝ ለአርሶ አደሩ የሚደረገው የድጋፍና ክትትል ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ማስገንዘባቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.