የ10 ዓመት የልማት ዕቅድ መካከለኛ ጊዜ አፈጻጸም ግምገማ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የ10 ዓመት የልማት ዕቅድ መካከለኛ ጊዜ አፈጻጸም ግምገማ ማጠናቀቂያ ላይ አቅጣጫዎችን አስቀመጡ፡፡
የ10 ዓመት የልማት ዕቅድ መካከለኛ ጊዜ አፈጻጸም ግምገማ በትናንትናው ዕለት መጀመሩ ይታወሳል፡፡
በዚህም የሁለተኛው የመካከለኛ (2016-2018) ዕቅድ የተገመገመ ሲሆን÷ የ2016 ዋና ዋና አቅጣጫዎችም በመድረኩ ታይተዋል፡፡
በመድረኩ አጠቃላይ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እና የሚሰሩ ሥራዎች ምን ዓይነት ቅርጽ እና መልክ አላቸው በሚለው ላይ ምክክር መደረጉም ተጠቁሟል፡፡
በዛሬው ዕለትም የ10 ዓመት የልማት ዕቅድ መካከለኛ ጊዜ አፈጻጸም ግምገማ መድረክን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ አጠናቅቀዋል፡፡