Fana: At a Speed of Life!

የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ለስድስት ክልሎች 11 ተሽከርካሪዎችን አበረከተ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከፊንላንድ መንግሥት ባገኘው ድጋፍ 11 ተሽከርካሪዎችን ለስድስት ክልሎች በድጋፍ አበረከተ።

ተሽከርካሪዎቹ ለአማራ፣ ለኦሮሚያ፣ ለሲዳማ፣ ለደቡብ ምዕራብ፣ ለቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልልና ለማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ነው በድጋፍ የተሰጡት።

የተሽከርካሪዎቹ ድጋፍ በፊንላንድ መንግሥት የመጠጥ ውኃ አገልግሎት ለማስፋት ለሚከናወነው የኮዋሽ ፕሮጀክት ማስፈጻሚያ የሚውል ነው ተብሏል።

የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ ፥ በዚሁ ጊዜ የፊንላንድ መንግሥት በዘርፉ የሚያደርገው ድጋፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል።

ተሽከርካሪዎቹ በተለያዩ አካባቢዎች የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ተደራሽ ለማድረግ የሚሰራውን ሥራ ውጤታማ ለማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽዖ ያደረጋል ነው ያሉት።

ድጋፍ የተደረገላቸው ክልሎች ተሽከርካሪዎቹ ለታለመላቸው ዓላማ እንዲያውሉ ጠይቀው ፥ የፊንላንድ መንግሥትም የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

ላለፉት 20 ዓመታት ሲተገበር የቆየው የኮዋሽ ፕሮጀክት በአሁኑ ሰዓት በሀገሪቱ በተለያዩ ክልሎች እየተተገበረ ሲሆን ፥ በዚህም 104 ወረዳዎችን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል።

በዚህም የኅብረተሰብ ክፍሎችን፣ ትምህርት ቤቶችንና ጤና ተቋማትን ንጹህ የመጠጥ ውሃና ንጽህና አጠባበቅ አገልግሎት ተጠቃሚ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.