የሬሜዲያል ፈተና በቅርቡ ስለሚሰጥ ተፈታኞች ዝግጅት እንዲያደርጉ ተጠየቀ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከነሐሴ 23 እስከ ነሐሴ 26 ቀን 2015 ዓ.ም ሊሰጥ የነበረው የሬሜዲያል ፈተና የተራዘመው የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ስላልተጠናቀቁ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
በሚኒስቴሩ የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ መጠናቀቅ ያለባቸው የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን በአግባቡ ለማጠናቀቅ ሲባል የፈተናውን ጊዜ ላልተወሰነ ጊዜ ማራዘም አስፈልጓል፡፡
የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እንደተጠናቀቁም በቅርቡ ተፈታኞች ለፈተና ስለሚጠሩ ዝግጅት እያደረጉ እንዲጠብቁ አሳስበዋል፡፡
ባለፈው ጊዜ ፈተና ያልወሰዱ እና የማካካሻ ትምህርት ሲከታተሉ የነበሩ 46 ሺህ የሚጠጉ የመንግሥትና የግል ተማሪዎች በቅርቡ ፈተናቸውን እንደሚወስዱ አረጋግጠዋል፡፡
በቅርቡ ፈተናቸውን የሚወስዱ እና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ የሚያመጡ የሬሜዲያል ተፈታኞችም ቀደም ብለው የሬሜዲያል ፈተና ወስደው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ካመጡ ተማሪዎች ጋር ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡበት ጊዜ ተመሳሳይ ስለሆነ ስጋት እንዳይገባቸው አስገንዝበዋል፡፡
በዮሐንስ ደርበው
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!