Fana: At a Speed of Life!

የዋግነር መሪ በተሳፋሪ ዝርዝር ውስጥ ያለበት አውሮፕላን ተከሰከሰ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሞስኮ በስተሰሜን አቅጣጫ ዛሬ በተከሰከሰው የግል አውሮፕላን ውስጥ የሩሲያ ቅጥረኛ ወታደሮች ዋና አዛዥ ዪቭጌኒ ፕሪጎዢን በተሳፋሪ ዝርዝር ውስጥ መኖሩ እየተነገረ ነው፡፡

ከተከሰከሰው የግል አውሮፕላን ውስጥ ተሳፍረው ከነበሩ መንገደኞች ዝርዝር ውስጥ የዋግነሩ መሪ ስሙ መኖሩን አልጀዚራ የሩሲያ አቪዬሽን ባለስልጣንን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡

አውሮፕላኑ በተከሰከሰበት ቦታ እስካሁን ድረስ 8 አስከሬኖች መገኘታቸውን የድንገተኛ አደጋ አገልግሎቱን ጠቅሶ የሩሲያ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን (ሪያ) መዘገቡን አልጀዚራ አመላክቷል፡፡

ምንም እንኳን የሩሲያ አቪዬሽን ባለስልጣን በተሳፋሪዎች ዝርዝር ውስጥ የዋግነር መሪ እንዳለ ቢገልጽም÷ በተከሰከሰው አውሮፕላን ውስጥ ፕሪጎዢን ስለመኖሩ ማረጋገጫ አለመኖሩ ነው የመለከተው፡፡

የሩሲያ የአደጋ ጊዜ ጉዳዮች ሚኒስቴር ቀደም ብሎ በሰጠው መግለጫ÷ ከሞስኮ ወደ ሴንት ፒተርስበርግ ሲበር በነበረ የግል አውሮፕላን ውስጥ 10 ሰዎች ተሳፍረዋል ብሏል። አሁንም የነፍስ አድን ሥራው ተጠናክሮ መቀጠሉን ነው ኤጀንሲው ያስታወቀው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.