Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ የ2016 ትምህርት ዘመን የትምህርት ጉባዔ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2016 ትምህርት ዘመን የትምህርት ጉባዔ መካሄድ ጀምሯል፡፡

ጉባኤው “ሁለንተናዊ ርብርብ ለትምህርት ተቋማት ደረጃ መሻሻል” በሚል መሪ ሃሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲበ አዳነች አቤቤ ጉባኤውን ሲያስጀምሩ እንዳሉት÷ መድረኩ የ2015 የትምህርት ዘመን ድክመትና ጥንካሬዎች የሚለዩበትና ትውልድን በዕውቀትና በስነ ምግባር የማነጹ ስራ ያለበት ደረጃ የሚገመገምበት ነው፡፡

ከዚህ ባለፈም ጥንካሬዎች ይበልጥ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ድክመቶች ደግሞ መንስዔዎቻቸው ተለይተው የሚታረሙበት አቅጣጫ የሚቀመጥበት እንደሆነም አንስተዋል፡፡

በ2015 የትምህርት ዘመን የተመዘገቡ የተሻሉ ውጤቶች እና ፍሬዎቻችው ተስፋ ሰጪ እንደሆኑም ከንቲባዋ ጠቅሰዋል፡፡

“ይሁን እንጂ በተሰራው እና በተሳካው ሳንረካ ለበለጠ ድል ዝግጅት ለማድረግ ጉባዔው ጠቃሚ ሀሳቦችን እንደሚያነሳ ተስፋ አደርጋለሁ” ብለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.