በ886 ሚሊየን ብር የተገዙ የፍሳሽ ማስወገጃ ተሽከርካሪዎችና ሌሎች እቃዎች ለከተሞች ተሰጡ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በ886 ሚሊየን ብር ወጪ የተገዙ 25 የፍሳሽ ማስወገጃ ተሽከርካሪዎች እና ሌሎች የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን እቃዎችን ለተለያዩ ከተሞች አስረክቧል።
በሚኒስቴሩ የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ ተሽከርካሪዎቹን ለየከተሞቹ የውሃና ፍሳሽ ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች አስረክበዋል።
በሁለተኛው የከተሞች መጠጥ ውኃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት የከተሞች ፍሳሽ አወጋገድ ስርዓትን ለማሻሻል በአጭር፣ በመካከለኛና በረጅም ጊዜ መፍትሔ ለመስጠት ጥናት መካሄዱ ተገልጿል፡፡
በጥናቱ መሰረትም የከተሞችን የፍሳሽ አወጋገድ ለማሳለጥ የሚያግዙ 264 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው 25 የፍሳሽ ማስወገጃ መኪናዎች ለ8 ከተሞች መበርከታቸው ተጠቁሟል፡፡
በተጨማሪም 622 ነጥብ 1ሚሊየን ብር ወጪ የተደረገባቸው የውሃ ብክነትን የሚቀንሱ መገጣጠሚያዎች፣ ቆጣሪዎች፣ የውሃ ቆጣሪ ልኬት ማስተካከያዎች እና ሌሎች እቃዎች ለ22 ከተሞች ተሰጥተዋል፡፡
አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ÷ የፍሳሽ ማስወገጃ ተሽከርካሪዎች እና ሌሎች እቃዎች ለታለመላቸው አላማ ብቻ ሊውሉ እንደሚገባ መናገራቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
ሁለተኛው የከተሞች የመጠጥ ውሃ ሳኒቴሽን ፕሮጀክት የከተሞችን የፍሳሽ አወጋገድ ስርዓት ለማሳለጥ ለአምስት አመት የሚተገበር ፕሮጀክት ነው።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!