ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ የአካባቢ ፋሲሊቲ የሃብት አመዳደብ ቀመር የሀገራትን ወቅታዊ ነባራዊ ሁኔታ ታሳቢ እንዲያደርግ ጠየቀች
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ የአካባቢ ፋሲሊቲ የሃብት አመዳደብ ቀመር የሀገራትን ወቅታዊ ነባራዊ ሁኔታ ታሳቢ እንዲያደርግ ጠይቃለች፡፡
በካናዳ ቫንኮቨር የዓለም አቀፍ የአካባቢ ፋሲሊቲ ጉባዔ እየተካሄደ ነው፡፡
የኢትዮጵያን ልዑካን ቡድን እየመሩ የኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ጌታሁን ጋረደው(ዶ/ር) እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡
ዋና ዳይሬክተሩ በዚህ ወቅት ፥ በመንግስት ቁርጠኛ አመራር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሸለ የመጣውን የኢትዮጵያ የፕሮጀክቶች አፈጻጸምንም ነው ያነሱት፡፡
በዚህም የዓለም አቀፍ የአካባቢ ፋሲሊቲ የሃብት አመዳደብ ቀመር ከፈረንጆቹ 2017 በፊት ባለው መረጃ የተመሰረተ የሀገራት የፕሮጀክት አፈጻጸም በመሆኑ እንደኢትዮጵያ ያሉ ጉዳዩን በመቀየር ያሉ ሀገራትን ተጎጂ እያደረገ መሆኑን አብራራርተዋል፡፡
ስለሆነም የፋሲሊቲው የሃብት አመዳደብ ቀመር የሀገራትን አሁናዊ ሁኔታ ከግምት ውስጥ ያስገባ እንዲሆን ማሳሰባቸውን ከባለስልጣኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ኢትዮጵያ የፋሲሊቲው የሃብት አመዳደብ ቀመር ከሙቀት አማቂ ጋዞች ልቀት ባሻገር የሀገራትን የአየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭነትን በአግባቡ ከግምት ውስጥ እንዲያስገባ ጠይቃለች፡፡
በተጨማሪም ፥ ታዳጊ ሀገራት የአየር ንብረት ለውጥን ተፅዕኖ ለመቋቋም የሚያደርጉትን ጥረት የበለጠ እንዲያግዝም ነው ያሳሰቡት፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!