Fana: At a Speed of Life!

3 ነጥብ 8 ሚሊየን ሄክታር መሬት በዘመናዊ የግብርና መሳሪያ መታረሱ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በተያዘው የመኸር ወቅት እስካሁን 3 ነጥብ 8 ሚሊየን ሄክታር መሬት በዘመናዊ የግብርና መሳሪያ መታረሱን የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ለፋና ብርድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ በ2014/15 የመኸር ወቅት 2 ነጥብ 9 ሚሊየን ሄክታር መሬትን በሜካናይዜሽን ማልማት ተችሏል፡፡

ዘመናዊ የግብርና መሳሪያዎችን ለአርሶ አደሩ ተደራሽ ለማድረግ የተለያዩ የፖሊሲ አማራጮች ተዘርግተው እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ማንደፍሮ ንጉሴ (ዶ/ር) በበኩላቸው÷ የትራክተርና ኮምባይነር ቁጥርን በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ17 ሺህ በላይ ማድረስ እንደተቻለ ተናግረዋል፡፡

10 የሜከናይዜሽን አገልግሎት ማዕከላትም በተለያዩ ክልሎች የማቋቋም ስራ እየተሰራ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡

እስካሁንም አራት ማዕከላትን ወደ ስራ ማስገባት መቻሉን ተናግረዋል፡፡

በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት ከ 142 ሺህ በላይ ትራክተሮችንና ከ46 ሺህ በላይ ኮምባይነሮችን ለአርሶ አደሩ ለማሰራጨት እቅድ ስለመያዙም አመከላክተዋል፡፡

በዙፋን ካሳሁን

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.