የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም አፍሪካ የማካካሻ በጀት ያሻታል – ኢጋድ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን ለመከላከል እና ለመቋቋም አፍሪካ የማካካሻ በጀት እንደሚያሥፈልጋት የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ-መንግሥታት (ኢጋድ) አስታወቀ፡፡
የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል አፍሪካ-መር የባለ-ብዙ ወገን ትብብር እንደሚያሻም አስገንዝቧል፡፡
በኢጋድ ዋና ሥራ አሥፈፃሚ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) የሚመራው ልዑክ በአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ ላይ ይሳተፋል፡፡
ምንም እንኳን አፍሪካ ለዓለም ሙቀት መጨመር የምታበረክተው አስተዋፅዖ እዚህ ግባ የሚባል ባይሆንም ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዙ አደጋዎች ስትጠቃ መቆየቷ አፅንዖት ተሠጥቶት ለጉዳቷ የሚገባትን ማካካሻ እንድታገኝ እንደሚጠየቅ ከኢጋድ ቃል-አቀባይ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ ከፈረንጆቹ መስከረም 4 – 8 ፣ 2023 በናይሮቢ ኬንያ ይካሄዳል፡፡