Fana: At a Speed of Life!

የደመና ማልማት ቴክኖሎጂ አበረታች ውጤት ማስመዝገቡ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ድሮን በመጠቀም፣ በግራውንድ ጀኔሬተር እና የርቀት መቆጣጠሪያን በመጠቀም ዛሬ የተደረገው የደመና ማዝነብ ቴክኖሎጂ ሙከራ ውጤታማ መሆኑ ተገለጸ፡፡

የመስኖ እና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አይሻ መሀመድ (ኢ/ር) በሙከራ መርሐ ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር ዝናብ አጠር እና ቆላማ የሆኑ አካባቢዎች የድርቅ ችግር ሰላባ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

ይህ ቴክኖሎጂ በዘርፉ ያለውን ችግር ለመፍታት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው ብለዋል።

የመስኖ እና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ለደመና መልማት የሚያስፈልጉ 60 ግራውንድ ጀኔሬተሮችን ለማሰራት ድጋፍ ማድረጉ በትብብር የመስራታችን ጅማሮ ነው ሲሉም ገልጸዋል።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ሰለሞን ሶካ በበኩላቸው÷ በቀጣይ የደመና ማልማት ፕሮጀክት ሰፊ ቦታዎችን በሸፈነ መልኩ እንዲሰራበት የሚያስችሉ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን አንስተዋል።

የደመና ማልማት (Cloud Seeding) ቴክኖሎጂ ደመናን የማዝነበ ሂደት ሲሆን÷ በአየር ላይ ተንሳፎ የሚገኝ ደመና ውስጥ የሚገኝን እርጥበት ወደ መሬት በዝናብ መልክ የማውረድ ቴክኖሎጂ ነው፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.