Fana: At a Speed of Life!

በዚህ ዓመት 5 የኳራንታይን ጣቢያዎች ተለይተው የሚያስፈልጋቸውን መሳሪያዎች ለማሟላት ፈቅደናል – አቶ ካሳሁን ጎፌ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዚህ የበጀት ዓመት አምስት የሚጠጉ የኳራንታይን ጣቢያዎች ተለይተው የሚያስፈልጋቸውን ማሸነሪና መሳሪያ ለማሟላት በስትሪንግ ኮሚቴ ፈቅደናል ሲሉ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴዔታ ካሳሁን ጎፌ ተናገሩ።

የኳራንቲን ጣቢያዎች የቁም እንስሳት ጥራት ከበሽታ ነፃ የሆኑ፣ የተቀባይ ሀገራትን ደረጃ ያሟሉና በትክክለኛ መስፈርት ለገበያ ለማቅረብ ወሳኝ ናቸው ተብሏል።

በመሆኑም የኢትዮጵያን የቁም እንስሳት የወጪ ንግድ ለማሳለጥ የሚሌ የኳራንቲን ጣቢያ በቅርቡ ስራ መጀመሩ ይታወቃል።

ከሚሌ በተጨማሪ በቀጣዩ የበጀት ዓመት አምስት የሚጠጉ የኳራንታይን ጣቢያዎች ተለይተው የማሸነሪና መሳሪያ ማሟላት ስራ የሚከናወን መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የቁም እንስሳትን ወደ ውጭ በመላክ የውጭ ምንዛሪ ገቢን ለማሳደግ መንግስት ሲሰራ መቆየቱንም መግለጻቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡

በዚህም የሚሌ ኳረንቲን ጣቢያ የኢትዮጵያ ኦሪጂን ኦፍ ሰርተፊኬት ያላቸውን የቁም እንስሳት ወደ ውጭ ሀገራት መላክ ተጀምሯል ነው ያሉት።

የቁም እንስሳት ቀደም ሲል በጅቡቲ ኳራንቲን ወደ ውጭ ሀገራት ይላክ እንደነበር አስታውሰው፥ ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚሌ ኳራንቲን ከ7 ሺህ በላይ በጎችን ወደ ሳዑዲ አረቢያ መላክ ተችሏል ብለዋል።

የሚሌ ኳራንቲን ወደ ስራ መግባቱ በቁም እንስሳት ሃብት የሚስተዋለውን ኮንትሮባንድ በማስቀረት ረገድ የላቀ ጠቀሜታ ያለው መሆኑንም ነው የተናገሩት።

ኢትዮጵያ በእንስሳት ሃብት ልማት የውጭ ምንዛሪ በማግኘት በዘርፉ ተጠቃሚነቷ እንዲያድግ ለማስቻል ከሚሌ በተጨማሪ በቀጣዩ ዓመት አምስት ጣቢያዎችን የመገንባት እቅድ መኖሩን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ በእንስሳት ሃብት ልማት የውጪ ምንዛሪ በማግኘት በዘርፉ ተጠቃሚነቷ እንዲያድግ ለማስቻል ከሚሌ በተጨማሪ በቀጣዩ ዓመት አምስት የኳራንታይን ጣቢያዎች ተለይተው የሚያስፈልጋቸው የማሸነሪና መሳሪያ ማሟላት በስትሪንግ ኮሚቴ ፈቅደናል ብለዋል።

ለመገንባት የሚያስፈልጋቸውን መሳሪያ ለማሟላት ከግብርና ሚኒስቴር ጋር በቅንጅት በመስራት ላይ መሆናቸውንም ነው ያነሱት፡፡

ከሳኡዲ በተጨማሪ ወደ ግብጽ፣ ኦማን፣ ጅቡቲ እና የመን ከሚሌ ኳራንቲን የቁም እንስሳትን ለመላክ ከሀገራቱ ጋር ንግግር እየተደረገ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.