Fana: At a Speed of Life!

የባሕር ዳር ከተማ የሰዓት እላፊ ገደብ ተሻሻለ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የባሕር ዳር ከተማ ሰላም በመሻሻሉ የተጣለው የሰዓት እላፊ ገደብ መሻሻሉ ተገለጸ፡፡

የባሕር ዳር ከተማ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት በከተማው ላይ የነበረውን የመንቀሳቀስ የሰዓት ገደብ ከዛሬ ነሐሴ 28 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ምሽቱ 2:00 ድረስ እንዲሆን ማሻሻሉን አሚኮ ዘግቧል፡፡

በተመሳሳይ ጎንደር ከተማ ወደ ሰላም መምጣቷን ተከትሎ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተጣለው የሰዓት ገደብ እስከ ምሽቱ 1 ሰዓት የነበረው የተሽከርካሪና የሰዎች እንቅስቃሴ እሰከ ምሽቱ 2 ሰዓት መሻሻሉን የከተማ አሥተዳደሩ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።

በከተማዋ አንጻራዊ ሰላም እንዲመጣና የሰዓት ገደቡ እንዲሻሻል የከተማዋ ወጣቶችና ነዋሪዎች ከፍተኛ እገዛ ማድረጋቸው ተነስቷል።

በቀጣይም በኮማንድ ፖስቱ ግምገማ የሚስተካከሉ ክልከላዎች ላይ መሰረት ተደርጎ ማሻሻዎች እንደሚኖሩ ከአማራ ኮሙኒኬሽን ያገኘው መረጃ አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.