የአፍሪካ ህብረት አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ፎረም በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 2ኛው የአፍሪካ ህብረት አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ዓመታዊ ፎረም በአዲስ አበባ ከተማ መካሄድ ጀምሯል፡፡
ፎረሙ በአፍሪካ ህብረት ኢኮኖሚ ፣ንግድና ቱሪዝም ዲፓርትመንት አማካይነት ነው የተዘጋጀው ፡፡
ፎረሙ በተለይም ጀማሪ ስራ ፈጣሪ ወጣቶች በክህሎት እና ሥራ ፈጠራ እንዲበረታቱ የሚያስችሉ ፖሊሲዎችን ለመቅረፅ ያለመ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
ባለሃብቶች በተለያዩ ኩባንያዎች ላይ መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ለማድረግ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ለኢንተርፕራይዞች ድጋፍ እንዲሰጡ ለማድረግ እንደሚያስችልም ተጠቁሟል፡፡
ኢንተርፕራይዞች አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች፣ ምርቶች እና አገልግሎቶችን ለማስተዋወቅ ከፍተኛ ሚና የሚጫወቱ መሆኑም ተገልጿል፡፡
ፎረሙ በአዲስ አበባ የህብረቱ አዳራሽ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ፈረንጆቹ መስከረም 8 ቀን ድረስ ለአምስት ቀናት እንደሚካሄድ የአፍሪካ ህብረት የተመድ የልማት ፕሮግራም መረጃ ያመላክታል፡፡