የከተማ አስተዳደሩ 1ሺህ 686 ቤቶችን ለአቅመ ደካሞችና ለሀገር ባለውለታዎች እያስረከበ ነው
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተደደር 1ሺህ 686 ቤቶችን ለአቅመደካማና ለሀገር ባለውለታዎች እያስረከበ ይገኛል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንደገለጹት ፥ በዛሬው ዕለት ለከተማዋ አቅመ ደካሞችና የሀገር ባለውለታዎች በተለያዩ ክፍለ ከተሞች የቤት ርክክብ እየተደረገ ነው፡፡
በመተላለፍ ላይ የሚገኙት ቤቶች ደረጃችውን የጠበቁና መገልገያ እቃ የተሟላላቸው መሆናቸውን ከንቲባዋ ገልጸዋል፡፡
የቤት ስጦታው ለከፍተኛ ማህበራዊ ችግር የተጋለጡ አቅመደካማ ነዋሪዎች አዲሱን ዓመት በአዲስ ቤት ፤ በአዲስ ተስፋ በደስታ እንዲቀበሉ እንደሚያስችሏቸው ተገልጿል፡፡
ለቤቶቹ ፕሮጀክት እገዛ ላደረጉ ባለሃብቶችና የከተማዋ ነዋሪዎችም ከንቲባ አዳነች ምስጋና አቅርበዋል፡፡
#Ethiopia #Addisabeba
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!