አፍሪካ ዓለምን ከካርበን ነፃ የማድረግ አቅም አላት – ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አፍሪካ ዓለምን ከካርበን ነፃ የማድረግ እና በአህጉሪቱ ኢንቨስትመንቶችን ለማሳደግ የሚያስችል አቅም አላት ሲሉ የኬኒያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ተናገሩ።
ፕሬዚዳንቱ በኬኒያ ለሶስት ቀናት በሚካሄደው የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ላይ እንደተናገሩት÷ አፍሪካ የአፍሪካን የአየር ንብረት ድርድር ለመቀየር እድሉን መጠቀም አለባት ብለዋል።
በአየር ንብረት ላይ ያተኮረ ውይይት በዓለም አቀፍ ደረጃ መካሄድ ከጀመረ ከሦስት አስርት ዓመታት በላይ ቢሆንም የአፍሪካ ሀገራት በአጀንዳው ላይ ለመወያየት አህጉራዊ ስብሰባ ሲያደርጉ ይህ የመጀመሪያው ነው።
ባለፉት ዓመታት የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ለውጥ ማዕቀፍ አካል በሆኑት እንደ የአፍሪካ ቡድን ተደራዳሪዎች እና የቡድን 77 አባል በሆኑ ቀጠናዊ ቡድኖቿ በኩል በዓለምአቀፍ የአየር ንብረት ጉባኤ ላይ አፍሪካ ስጋቷን መግለጿን አንስተዋል።
በአጠቃላይ ከሚለቀቀው በካይ ጋዝ ውስጥ ቢበዛ 4 በመቶው ብቻ ከአፍሪካ እንደሆነ ገልጸው፤ ከፍተኛ መጠን ያለው በካይ ጋዝ በሚለቁ ሀገራት በኩል ተጠቂ ለሆኑ ሀገራት ካሳ ለመስጠት የሚገቡ ቃሎችም ፍትሃዊ ባልሆነ አግባብ ችላ ይባላሉ ነው ያሉት፡፡
አፍሪካ ከአየር ንብረት ጉዳይ ጋር በተያያዘ የሚኖራትን መስተጋብር ጊዜ ሳይሰጠው መቀየርና መሻሻል እንደሚገባው ሩቶ ተናግረዋል፡፡
ለአየር ንበረት የሚያስፈልግ በቂ የገንዘብ አቅም እንደሌለን በግልፅ ተረድተናል ያሉት ፕሬዚዳንቱ÷ ነገር ግን አዎንታዊ ለውጥ ማምጣት ከሚችሉ እውነታዎች ፈቀቅ አንልም ሲሉ አክለዋል፡፡
የአየር ንብረት ለውጥ ረቂቅ ፅንሰ-ሀሳብ ሳይሆን በሳይንስ የተረጋገጠ እና በተግባርም የታየ በመሆኑ የተሰባሰብነው ችግሮችን ለመዘርዘር ሳይሆን በመፍትሄ ሀሳቦች ላይ ለመምከር ነው ማለታቸውን ዘ ኢስት አፍሪካን ዘግቧል፡፡
ዓለምን ከካርበን ነፃ ማድረግን በተመለከተም÷ አፍሪካ ከአህጉሪቱ ውጭ ያሉ ሌሎች ህዝቦችን ተጠቃሚ የሚያደርግ እና የልማት ገቢን መሰብሰብ የሚያስችል ታዳሽ ኃይልን መጠቀም አለባትም ብለዋል፡፡edited 12:02