በሀረሪ ክልል በ100 ሚሊየን ብር የተገነቡ የልማት ፕሮጀክቶች ተመረቁ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀረሪ ክልል በ100 ሚሊየን ብር የተገነቡ የልማት ፕሮጀክቶች ተመርቀዋል፡፡
በክልሉ ገጠር ወረዳዎች የተገነቡትን ፕሮጀክቶች የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ መርቀዋቸዋል።
በኤረርና በሶፊ ወረዳዎች የተገነቡት የድልድይ፣ የንፁህ መጠጥ ውሃና የኤሌክትሪክ ፕሮጀክቶች የህዝቡን ጥያቄ የመለሱ ናቸው ተብሏል።
አቶ ኦርዲን÷ የክልሉ መንግስት ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በከተማና በገጠር ያለውን የልማት ፍላጎት ለማሟላት እንደሚሰራ አስታውቀዋል።
በተሾመ ኃይሉ