Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ክልል ከ71 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ ማቀዱን አስታወቀ

 

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ በ2016 በጀት ዓመት ከ71 ነጥብ 65 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ ማቀዱን አስታውቋል።

ቢሮው “ሠላም ለሁላችን፣ ፍቅር ለህዝባችን፣ ግብር ለእድገታችን” በሚል መሪ ሀሳብ የ2016 በጀት ዓመት ግብርን ለመሰብሰብና የአዲሱን ዓመት ለመቀበል ሙሉ ዝግጅት ማድረጉን አስታውቋል።

የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ሃላፊ አቶ ክብረት አሕመድ÷ የሕዝብን የመልማት ጥያቄ ለመመለስ ግብር በታማኝነት መክፈል ዋነኛው መፍትሄ መሆኑን አስገንዝበዋል።

የግብር አከፋፈል ስርዓትን በማዘመን የሕዝብን ጥያቄ ለመመለስ እንዲቻልና በራስ አቅም ለመልማት እንዲሁም በባለቤትነት መሥራት ከሁሉም የሚጠበቅ በመሆኑ ሁሉም የድርሻውን መወጣት ይጠበቅበታል ብለዋል፡፡

ከከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች፣ ባለሙያዎችና ግብር ከፋዩን ጨምሮ ሁሉም በትብብር ሊሰራ እንደሚገባም ገልጸዋል፡፡

ቢሮው በ2015 በጀት ዓመት ከ42 ቢሊየን ብር በላይ ለመሰብሰብ አቅዶ ከ38 ቢሊየን ብር በላይ በመሰብሰብ የእቅዱን 88 ነጥብ 82 በመቶ ማሳካቱን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አስታውሷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.