Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮ-ሶማሊያ የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን የከፍተኛ ባለስልጣናት ስብሰባ በሞቃዲሾ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮ-ሶማሊያ የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን የከፍተኛ ባለስልጣናት ስብሰባ ዛሬ በሞቃዲሾ ተጀምሯል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀነራል አምባሳደር ፍስሃ ሻውል በመክፈቻ ላይ፥ ሁለቱ ሀገራት የመጀመሪያውን የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ስራዎች አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል፡፡

መድረኩ በየደረጃው ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት የበለጠ ተቋማዊ ለማድረግና አዳዲስ የትብብር መስኮችን ለመፈተሽ ያስችላልም ነው ያሉት።

አምባሳደሩ አክለውም ፥ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት በደም የተሳሰረ ወንድማማችነት መሆኑንም መናገራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የሶማሊያ የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስቴር ቋሚ ጸሃፊ ሃምዛ አዳን ሃዶው በበኩላቸው፥ የሁለትዮሽ ግንኙነቱ ፈተናውን ተቋቁሞ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ እና በማህበራዊ ዘርፎች ያለው ትብብር የበለጠ እንዲጠናከር ጥሪ አቅርበዋል።

#Ethiopia #Somalia #ethiosomalia #Somalia #JMC

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.