Fana: At a Speed of Life!

በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን መቅረፍ እንደሚጠበቅ ተመለከተ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአገልጋይነት ባህልን በማዳበር በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን መፍታት ይጠበቅብናል ሲሉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ-መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) አስገነዘቡ።

ዛሬ በሀገር አቀፍ ደረጃ የአገልጋይነት ቀን “ኢትዮጵያን እናገልግል” በሚል መሪ ሐሳብ እየተከበረ ነው፡፡

የ”አገልጋይነት ቀን”ን አስመልክቶ የክልሉ አመራሮችና ሰራተኞች በቦንጋ ከተማ የምክክር መድረክ አካሂደዋል።

ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) በመድረኩላይ ባደረጉት ንግግር ያለብንን ትልቅ ኃላፊነት በመረዳትና በገባነው ቃል መሰረት የአገልጋይነት ባህልን ማጎልበት ይገባናል ብለዋል።

በክልሉ አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ማታውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በአገልግሎት ሰጪው ዘንድ የአገልጋይነት ባህል መዳበር አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል ያግዛል ነው ያሉት፡፡

በተለይም ከማዘጋጃ ቤት፣ ከመታወቂያ አሰጣጥ፣ ከንግድ፣ ከግብር አሰባሰብና ሌሎች ለሙስና ተጋላጭ የሆኑ አገልግሎቶችን ከእጅ መንሻ ነፃ የማድረግ ስራ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባም ነው ያሳሰቡት፡፡

ለሕዝብ አገልግሎት የሚሰጠው የመንግስት ሰራተኛው ለኅሊናው ተገዝቶ ቀልጣፋ፣ ግልፅና ከአድልኦ የፀዳ አገልግሎት መስጠት ይገባዋል ያሉት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ÷ በዚህም በጋራ በመረባረብ ክልላችንና ሀገራችንን ወደ ተሻለ ደረጃ ማሻገር ይጠበቅብናል ሲሉ አስገንዝበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.