ርዕሰ መስተዳድሩ በተለይም የዓለም ቅርስ በሆነው የጁገል ቅርስ የፅዳት ስራዎችን ያከናወኑ ሲሆን÷ ነፃ የትራንስፖርት አገልግሎትንም አስጀምረዋል፡፡
አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ህብረተሰቡን በእኩልነት እና በፍትሃዊነት ማገልገል እንደሚገባቸውም አቶ ኦርዲን ተናግረዋል።
ከሙስና እና ብልሹ አሰራር የፀዳ ቀልጣፋ እና ዘመናዊ የአገልግሎት አሰጣጥ ተግባራዊ በማድረግ የህብረተሰቡን እርካታ ማሳደግ እንደሚገባ በአፅንዖት አሳስበዋል።
ማገልገል ትልቁ የአመራር ሚና መሆን አለበት ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ÷ ጷግሜን 1 የአገልጋይነት ቀንን በማስመልከት አመራሩ የተለያዩ አገልግሎቶችን ለሕዝብ ይሰጣል ብለዋል።
አገልጋይነት የአንድ ቀን ተግባር ብቻ ሳይሆን ዓመቱን ሙሉ ሊተገበር የሚገባው ስራ መሆኑንም ነው ርዕሰ መስተዳድሩ ያስገነዘቡት።
የዛሬውን የአገልጋይነት ቀን ምክንያት በማድረግ በክልሉ የሚገኙ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እስከ ምሽቱ 1 ሰዓት ድረስ አገልግሎት እንደሚሰጡ የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።edited 10:07