Fana: At a Speed of Life!

በኮምቦልቻ ከተማ የሚገኙ ተጠርጣሪዎች አገልግሎቶችን በጥሩ ሁኔታ እያገኙ እንደሆነ ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በምስራቅ አማራ ኮማንድ ፖስት በኮምቦልቻ ከተማ ጮሪሳ ጊዜያዊ ማቆያ የሚገኙ ተጠርጣሪዎች ሕክምናን ጨምሮ ሌሎች አገልግሎቶችን በጥሩ ሁኔታ እያገኙ መሆናቸውን ተናገሩ።

በማቆያው የፖሊስ አባላት ስነ- ምግባርን በተላበሰ መልኩ ኃላፊነታቸውን እየተወጡ መሆናቸውንም ነው ተጠርጣሪዎቹ ለኢዜአ የገለጹት፡፡

በማቆያው ያለው አያያዝ ሕግና ሥርአትን የተከተለና ሰብዓዊ መብታቸውን ያከበረ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡

ለአብነትም÷ የሕክምና አገልገሎት፣ ምግብ፣ ንጹሕ የማረፊያ ቦታ እና ሌሎች አስፈላጊ አገልገሎቶችን እያገኙ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ቤተሰቦቻቸው ተመላልሰው እየጠየቋቸው ስለመሆናቸውም አመላክተዋል፡፡

በአያያዛቸው ዙሪያ ያለው ጥሩ መሆኑን ጠቁመው የምርመራ ሂደቱ ግን መጓተቱን አንስተዋል፡፡

በመሆኑም ፖሊስ የምርመራ ሂደቱን አፋጥኖልን ፍርድ ቤት በመቅረብ የክስ ሂደታችንን እንድንከታተል ቢደረግ ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ አባል ሳዲቅ አደም÷ በማቆያ ማዕከሉ ለተጠርጣሪዎች የምግብ፣ የሕክምና፣ የጽዳት እንዲሁም የመኝታ አገልግሎት በተሟላ መልኩ እየቀረበ መሆኑን መመልከታቸውን ገልጸዋል።

የመርማሪ ቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ ነጃት ግርማ (ዶ/ር) በበኩላቸው÷ የተጠርጣሪዎች ሰብአዊ አያያዝ ጥሩ መሆኑን ተናግረዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.