Fana: At a Speed of Life!

የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሥርዓት ማሻሻያ ሪፎርም በተመረጡ ተቋማት ይተገበራል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በተያዘው በጀት ዓመት የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሥርዓት ማሻሻያ ሪፎርም በተመረጡ ተቋማት ተግባራዊ እንደሚደረግ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር መኩሪያ ኃይሌ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡

ሪፎርሙ በተለይ የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ በማሻሻል ረገድ የተሻለ ለውጥ እንደሚያመጣም አመልክተዋል።

ኮሚሽነሩ ይህን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀገራቸውን ከ38 ዓመታት በላይ ላገለገሉ ሰራተኞች እውቅና በሰጡበት ወቅት ባደረጉት ንግግር ነው፡፡

የመንግስት ተቋማት አሰራራቸውን በማዘመን ቀልጣፋ አገልግሎት ተደራሽ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸውም ነው የጠቆሙት፡፡

ለዚህም የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ስርዓት ማሻሻያ ሪፎርም መዘጋጀቱን ጠቅሰው፤ ለሪፎርሙ ማስፈጸሚያ የሚሆኑ የፖሊሲ ሰነድና ስትራቴጂዎች እንዲሁም የህግ ማእቀፎች በመጠናቀቅ ላይ ናቸው ብለዋል፡፡

ሪፎርሙ በኢትዮጵያ የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን በማዘመንና በማቀላጠፍ ረገድ መሰረታዊ ለውጥ እንደሚያመጣም አብራርተዋል፡፡

የሪፎርሙ የዝግጅት ሥራ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ስድስት ወራት ውስጥ እንደሚጠናቀቅም ጠቁመዋል፡፡

ይህን ተከትሎም በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን፣ በጤና ሚኒስቴር፣ በትምህርት ሚኒስቴር፣ በግብርና ሚኒስቴር፣ በፕላንና ልማት ሚኒስቴርና በገንዘብ ሚኒስቴር የሪፎርሙ ሙከራ ትግበራ ይካሄዳል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.