በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል “የመስዋዕትነት” ቀን እየተከበረ ነው
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል “የመስዋዕትነት” ቀን በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ነው።
ቀኑ እየተከበረ የሚገኘው “በመስዋዕትነት የምትጸና ሀገር!” በሚል መሪ ሐሳብ ነው፡፡
ስለሀገርና ሕዝብ መሥዋዕትነት የከፈሉ ጀግኖችን በማስታወስና ክብር በሚሰጡ ሁነቶች ቀኑ እየተከበረ መሆኑን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡
በአከባበሩ ላይ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን፣ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የመከላከያ ሠራዊት፣ የፌዴራል ፖሊስ፣ የክልሉ ፖሊስ እና የጸጥታ አመራሮች እንዲሁም የአሶሳ ከተማ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
በአሶሳ ከተማ በክልሉ ፖሊስ ማርች ባንድ የታጀበ የእግር ጉዞ እየተደረገ መሆኑም ተመላክቷል፡፡
በጉዞው ላይ “መነሻና መድረሻችን የኢትዮጵያ ክብር ነው”፣ “እንደቀደምት አባቶቻችን እኛም ኢትዮጵያችን ከፍ እናደርጋታለን” የሚሉ እና ሌሎች መልዕክቶች እየተላለፉ ይገኛል።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!