Fana: At a Speed of Life!

መስዋዕትነት የከፈሉ ጀግኖችን ማክበር ይገባል- አትሌት ቀነኒሳ በቀለ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሁሉም መስክ ለሀገራቸው መስዋዕትነት የከፈሉ ጀግኖችን ማክበር፣ ማመስገንና ተገቢውን ክብር መስጠት እንደሚገባ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ተናገረ።

አትሌት ቀነኒሳ ኢትዮጵያ በሁሉም የሙያ መስክ በርካታ ጀግኖች ማፍራቷን ገልጿል፡፡

በአትሌቲክስ ዘርፍ ሀገር ወክሎ መወዳደርና በግል መወዳደር ልዩነት እንዳለው ጠቁሞ÷ የሀገርን አርማ አጥልቆና ሰንደቅን ወክሎ መሮጥ የተለየ ኩራትና ክብር አለው ብሏል፡፡

በሁሉም መስክ ለሀገር መስዋዕትነት የከፈሉ አያሌ ጀግኖችን ማመስገን፣ ተገቢውን ክብርና ዕውቅና መስጠት እንደሚገባ አስግንዝቧል፡፡

ለሀገርና ለሕዝብ የማያልፍ ታሪክ ሰርቶ ማለፍ ትልቅ ክብርና አድናቆት የሚሰጠው መሆኑንም ነው የገለጸው፡፡

ኢትዮጵያውያን በሁሉም መስክ ለሀገር አንድነት፣ አብሮነትና እድገት በጋራ መሮጥ ይጠበቅብናል ማለቱን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የ2016 አዲስ ዓመት የሰላም የፍቅርና የአብሮነት እንዲሁም ለኢትዮጵያ የስኬት ዘመን ይሁን በማለት የመልካም ምኞት መልዕክቱን አስተላልፏል።

አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በኦሎምፒክ 3 ወርቅ፣ በዓለም ሻምፒዮና 5 ወርቅ፣ በዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና 1 ወርቅ፣ በአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና 2 ወርቅ፣ በመላው አፍሪካ ጨዋታዎች 2 ወርቅ፣ በዓለም አገር አቋራጭ 11 ወርቅ፣ በበርሊን ማራቶን በፈረንጆቹ 2016 እና 2019 2 የወርቅ ሜዳሊያዎችን ሰብስቧል፡፡

በዓለም አቀፍ ውድድሮች በድምሩ 26 የወርቅ ሜዳሊያዎችን በማግኘት የዓለም የውድድር ድምቀትና የኢትዮጵያ ኩራት መሆን የቻለ አትሌት ነው፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.