በአቶ ደመቀ መኮንን የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ሞቃዲሾ ገባ
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ሶማሊያ ሞቃዲሾ ገብቷል።
የልዑካን ቡድኑ ኤደን አዴ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ የሶማሊያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሣላህ አሕመድ ጃማ እና በሶማሊያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሙክታር መሃመድ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
ልዑኩ ሶማሊያ ሞቃዲሾ የተገኘው በመጀመሪያው የኢትዮ-ሶማሊያ የጋራ ሚኒስትር ኮሚሽን ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ እንደሆነ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም ዛሬ በኢትዮጵያ ዲፕሎማሲያዊ ጉዳዮች ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
ቃል አቀባዩ በመግለጫቸው እንዳስታወቁት ፥ ጉባዔው በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት እንደሚያሳድግ ጠቁመዋል።
የኢትዮጵያና ሶማሊያ የሁለትዮሽ ግንኙነት አሁን ያለበት ደረጃ የጠበቀ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነታቸውን ማሳያ እንደሆነም ነው የገለጹት።
ኢትዮጵያ የሁለትዮሽ ግንኙነቷን በፖለቲካዊ ብቻ ሳይሆን በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎችም ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ፍላጎት እንዳላትም አምባሳደሩ አንስተዋል።
ሁለቱ ሃገራት በንግድና መከላከያ ትብብር ላይ ሁለት ስምምነቶች እንዲሁም በሁለትዮሽ የፖለቲካ ምክክር ላይ የመግባቢያ ሰነድ ይፈራረማሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ጠቁመዋል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!