ኢትዮጵያ ለ78ኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ዝግጅት ማድረጓን አስታወቀች
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ለ78ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅት ማድረጓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም በኢትዮጵያ ዲፕሎማሲያዊ ጉዳዮች ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም ፥ በቅርቡ ስለሚካሄደው 78ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ተናግረዋል፡፡
አምባሳደሩ ፥ ጉባዔው በ174 አጀንዳዎች ላይ እንደሚመክር የገለጹ ሲሆን ፥ የኢትዮጵያ አቋም በ55ቱ እንደሚገለጽ መናገራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
በዚህም የኢትዮጵያ ቋሚ ሚስዮን ለጠቅላላ ጉባዔው አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት መደረጉን አንስተው ፥ ኢትዮጵያ በጉባዔው በከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እንደምትወከል ገልጸዋል፡፡
የ2030 የዘላቂ ልማት ግቦችን ጨምሮ የተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ከፈረንጆቹ መስከረም 18 እስከ 24 ቀን 2023 እንደሚወያዩም ጠቁመዋል፡፡
ከዚህ ባሻገር ከተለያዩ ሀገራት መሪዎችና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር የጎንዮሽ ስብሰባዎች ይካሄዳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ አምባሳደሩ በመግለጫቸው አንስተዋል፡፡
#Ethiopia #UN
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!