Fana: At a Speed of Life!

በጎነት መልሶ ለራስ የሚከፍል በመሆኑ ሁሉም ዜጋ የዕለት ተለት ተግባሩ ሊያደርገው ይገባል – ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጎነት መልሶ ለራስ የሚከፍል በመሆኑ ሁሉም ዜጋ የዕለት ተለት ተግባሩ አድርጎ በችግር ውስጥ የሚገኙ ወገኖችን መርዳት አለበት ሲሊ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ጳጉሜ 3 የበጎነት ቀን “በጎነት ለሀገር” በሚል መሪ ሃሳብ በመላ ሀገሪቱ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው።

ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ÷ ዕለቱን አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት በበጎነት ቀን ባህላችን የሆነውን በጎነት ከፍ አድርገን የምናሳይበት መሆን አለበት ብለዋል።

“ወቅቱ አዲስ ዓመት እንደመሆኑ በበአሉ የተቸገሩትን በመርዳትና በመደገፍ፣ በትምህርት ቤቶች አካባቢ የሚሰሩ ስራዎችን የምናጠናክርበት ሊሆን ይገባል” ብለዋል።

በተጨማሪም የአቅመ ደካሞችን ቤት የምንጠግንበት፣ ከተሞንችን የምናፀዳበት ባጠቃላይ በክረምት በጎ ፈቃድ የጀመርናቸውን በጎ ተግባራት የምናስቀጥልበት ሊሆን ይገባል ሲሉ ማስገንዘባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በጎነት መልሶ ለራስ የሚከፍል በመሆኑ ወጣቶች፣ የመንግስት መዋቅሮች፣ በአጠቃላይ ሁሉም ህብረተሰብ በጎነትን የእለት ተለት ተግባሩ አድርጎ በችግር ውስጥ የሚገኙ ወገኖችን ከችግራቸው ማውጣት እንደሚገባ አመልክተዋል።

የመደጋገፍና የመረዳዳት ተግባሩ በቀጣዮቹ በዓላት ቀንም ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አስታውቀዋል።

በተመሳሳይ የአዲስ ዓመት በዓልን ምክንያት በማድረግ ለ864 ታራሚዎች ይቅርታ መደረጉን የክልሉ ፍትሕ ቢሮ አስታውቋል፡፡

ይቅርታ የተደረገላቸውም በሚዛን ፣ቦንጋ፣ ታርጫ፣ አማያ ፣ ማሻ እና ቱም ማረሚያ ቤቶች የሚገኙ ታራሚዎች  መሆናቸው ተጠቅሷል፡

የእስራት ጊዜ ቅናሽ ከዕድሜ ልክ ወደ 25 ዓመት የተደረገላቸዉ 11 ታራሚዎች እንደሚገኙም ተመላክቷል፡፡

 

 

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.