Fana: At a Speed of Life!

የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ለ50 ሰራተኞቹ የበዓል ፍጆታ ምርቶች ድጋፍ አደረገ

 

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ከልህቀት የወጣቶች ማህበር ጋር በመተባበር ለ50 ሰራተኞቹ የበዓል ፍጆታ ምርቶች ድጋፍ አደረገ።

ዛሬ በመላ ሀገሪቱ “በጎነት ለሀገር” በሚል መሪ ሐሳብ የበጎነት ቀን በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል።

በዝግጅቱ ላይ ለሚኒስቴሩ ሰራተኞች የበጎነት ቀንን ምክንያት በማድረግ በጽዳትና በጥበቃ ስራ ላይ ለተሰማሩ 50 የተቋሙ ሰራተኞች እንደ ዘይትና ዱቄት ያሉ የበዓል ፍጆታ ምርቶች ድጋፍ ተደርጓል።

የከተማ ልማትና መሰረተ ልማት ሚኒስትሯ ጫልቱ ሳኒ በወቅቱ በጎነት ማሰባሰብና ማሻገር የሚችል ሀይል ነዉ ሲሉ ገልጸዋል።

በተቋሙ በተለያዩ ግዜ በደም ልገሳና በሌሎችም የማህበረሰብ አገልግሎቶች ሲሰራ የቆየው የበጎነት ተግባር ወደፊት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል።

በአሸናፊ ሽብሩ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.