Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ በተመሳሳይ የጥራት ደረጃ ትምህርትን ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2016 የትምህርት ዘመን የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥና ተደራሽነትን ለማስፈን ትኩረት ተደርጎ እንደሚሰራ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።

ቢሮው የ2016 የትምህርት ዘመን አጀማመርን አስመልክቶ ከርዕሳነ መምህራን ጋር ውይይት አድርጓል፡፡

የቢሮው ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) በውይይቱ ላይ እንደገለፁት÷ ነጻ፣ ፍትሐዊ እንዲሁም ሠላማዊ የመማር ማስተማር እንዲጠናከርና የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል እየተሠራ ነው፡፡

ከፍትሐዊነት አንጻር ለአካል ጉዳተኞችና ሴቶች በሁሉም የከተማዋ አካባቢዎች በተመሳሳይ የጥራት ደረጃ የትምህርት አገልግሎት ተደራሽ የማድረግ ስራ በልዩ ትኩረት እየተከናወነ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የተማሪዎችን ውጤትና ሥነ- ምግባር ማሻሻል ለትምህርት ሥርዓቱ ወሳኝ ስለሆነ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ውጤታማ የመማር ማስተማር ስራ ለማከናወን በየትምህርት ተቋማቱ ስጋት የሚሆኑ ጉዳዮችን በመለየት አስቀድሞ መከላከል እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡

ባለፋት ሁለት ወራት ትምህርት ቤቶችን ለመማር ማስተማር ስራ ምቹ የማድረግ ስራ ሲሰራ መቆየቱን በማስታወስም፥ መስከረም 7 ቀን 2016 ዓ.ም መደበኛ ትምህርት እንደሚጀመር አስረድተዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.