Fana: At a Speed of Life!

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል ፈተናን ያላጠናቀቁ ተማሪዎችን አስፈትኖ ማጠናቀቁን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጸጥታ ችግር የ12ኛ ክፍል ፈተናን ያላጠናቀቁ ተማሪዎችን በሰላም አስፈትኖ ማጠናቀቁን የጎንደር ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ።
11 ሺህ 851 ተማሪዎች መስከረም 10 እና 11 ቀን 2016 ዓ.ም በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በሰላም ፈተናቸውን ማጠናቀቃቸውን የዩኒቨርሲቲው አሥተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዚዳንት ልጃለም ጋሻው ገልጸዋል።
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለተፈታኝ ተማሪዎች ቀደም ብሎ የሥነ ልቦናና የማረጋጋት ሥራዎችን በየትምህርት ቤታቸው ሲሰጥ መቆየቱን የጠቀሱት አቶ ልጃለም ወደ ዩኒቨርሲቲው ከገቡ በኋላም አስፈላጊው ዝግጅት ሁሉ ተደርጎ ተማሪዎች በተረጋጋ መንፈስ ፈተናቸውን በሰላም አጠናቀዋል ብለዋል።
ፈተናው በሰላም ተጀምሮ በአግባቡ እንዲጠናቀቅ እና ትብብር ላደረጉ አካላትና ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አቶ ልጃለም አመስግነዋል።
ተፈታኝ ተማሪዎችም ፈተናው በሰላምና በተረጋጋ ኹኔታ መጠናቀቁን መናገራቸውን አሚኮ ዘግቧል።
በሀገር አቀፍ ፈተናዎች አገልግሎት የፈተና ጣቢያ ኃላፊ አቶ ወንድወሠን ሽፈራው የተማሪዎች ፈተና ቶሎ ታርሞ ውጤቱ ይፋ እንደሚደረግ መረጃ እንዳላቸው ጠቁመዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.