Fana: At a Speed of Life!

1 ሺህ 498ኛው የመውሊድ በዓል እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 16 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 1 ሺህ 498ኛው የመውሊድ በዓል በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ ነው።

በዓሉ በተለይም በታላቁ አንዋር መስጂድ በታላቅ ድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

በዓሉ የሃይማኖት አባቶች፣ የእምነቱ ተከታዮች፣ አምባሳደሮች፣ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ከማለዳው ጀምሮ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስነ-ስርዓቶች ነው እየተከበረ የሚገኘው።

በዓሉን የታላቁ አንዋር መስጂድ ኢማም ሸህ ጣኻ ሀሩን ቁርአን በመቅራትና ዱዓ በማድረግ አስጀምረውታል።

የመውሊድ በዓል በነቢዩ መሐመድ መልካም ተግባራትን የህይወት መርህ አድርጎ ለማስቀጠል የሚከበር በዓል መሆኑ ኢማሙ ተናግረዋል።

በህይወት ዘመናቸው ለእምነቱ መፅናት የከፈሉትን መስዋዕትነት ለማሰብ፣ የሰላም፣ የፍትሕ፣ የዕኩልነትና የበጎነት አስተምህሯቸውን ለመከተል፣ እርሳቸውንና ተከታዮቻቸውን ለማወደስ የሚከበር መሆኑንም ነው ኢማኑ የተናገሩት።

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ሼህ ፈቱዲን ሀጂ ዘይኑ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመራኦል ከድር

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.