የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ አባላት ተልዕኳቸውን በታማኝነት መፈጸም ይጠበቅባቸዋል- ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ አባላት በተሰማሩበት መስክ የሚሰጣቸውን ተልዕኮ በቅንነትና ታማኝነት መፈጸም እንደሚጠበቅባቸው ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ገለጹ፡፡
የኮማንዶ እና አየር ወለድ ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከላት አመራሮች እና አሰልጣኞችን አቅም ለማሳደግ የአሰልጣኞች ስልጠና እየተካሄደ መሆኑን የመከላከያ ሠራዊት መረጃ ያመላክታል፡፡
የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፈልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በስልጠናው ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ጠንካራ እና ፕሮፌሽናል የመከላከያ ሠራዊት ለመገንባት ወታደራዊ አሰልጣኞች አርአያ መሆን ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡
ስለጠናው በኮማንዶ እና አየር ወለድ ዕዝ ስር የሚገኙ የኮማንዶ፣ የአየር ወለድ እና የልዩ ኃይል ጸረ ሽብር ማሰልጠኛ ማዕከላትን አቅም ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ ያለመ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡