ፖሊስ የተሰረቁ 9 ተሽከርካሪዎችን ለባለቤቶቻቸው እንዲመለሱ ማድረጉን ገለጸ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ፖሊስ ባደረገው ጥናትና ክትትል በተለያየ ጊዜ የተሰረቁ ዘተኝ ተሽከርካሪዎችን በመያዝ ለባለቤቶቻቸው እንዲመለሱ ማድረጉን አስታውቋል፡፡
በወንጀሉ የተለያየ ድርሻ ያላቸው 26 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውም ተገልጿል፡፡
በተወሰኑ ቀናት ብቻ ዘጠኝ ተሽከርካሪዎች ለባለቤቶቻቸው እንዲመለሱ ማድረጉን የገለጸው ፖሊስ÷ 3 ተሽከርካሪዎች ደግሞ ተፈታትተው በጋራዥ ውስጥ ተይዘዋል ብሏል፡፡
በወንጀሉ የተለያየ ተሳትፎ ያላቸው 26 ተጠርጣሪዎችም ተገቢው ምርመራ ተጣርቶ ክስ እንዲመሰረትባቸው ለሚመለከተው የፍትሕ አካል መዝገቡ ተልኳል ነው ያለው፡፡