Fana: At a Speed of Life!

ኢራናዊቷ ናርጌስ ሞሐመዲ የ2023 የኖቤል የሰላም ሽልማትን አሸነፈች

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 25 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2023 የኖቤል የሰላም ሽልማት ኢራናዊቷ ናርጌስ ሞሐመዲ አሸነፈች።
ናርጌስ ሞሐመዲ በሀገሯ ኢራን በሚገኘው ኤቪን በሚባለው ማረሚያ ቤት በእስር ላይ ትገኛለች።
ወጣቷ በሀገሯ የሰብአዊ መብት አቀንቃኝ እና የነፃነት ታጋይ መሆኗን የኖቤል ኮሚቴው መረጃ ያመላክታል።
ናርጌስ ኢራን ውስጥ ሰብአዊ መብት፣ ነፃነት እና ዴሞክራሲ እንዲከበር በምታደርገው ተጋድሎ ሽልማቱ እንደተበረከተላትም ነው የተነገረው።
ወጣቷ በሴቶች ላይ የሚደርሰው ጭቆና እንዲቆም የምታደርገውን ተጋድሎ ያደነቀው ኮሚቴው “የነፃነት ታጋይ” ነበረች ሲልም አሞካሽቷታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.