ርእሰ መስተዳድሩ በመልዕክታቸው ኢሬቻ የኦሮሞ ህዝብ ክረምቱን በሠላም ማለፉን፣ ከጨለማ ወደ ብርሃን በሰላም መሸጋገሩን፣ አዲስ ዓመት መበሰሩን መሠረት በማድረግ ለፈጣሪው ምስጋና የሚያቀርብበትና አክብሮቱን የሚገልፅበት በዓል ነው ብለዋል።
የኢሬቻ በዓል የኦሮሞ ሕዝብ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ወንድምና እህት ህዝቦች ጋር በሠላም፣ በፍቅር፣ በመቻቻልና በአብሮነት የሚያከብረው የአደባባይ በዓል መሆኑን በመጥቀስ ለመላው የኦሮሞ ህዝብ በዓሉ የፍቅር፣ የሠላም፣ የጤና፣ የመቻቻል እና የአብሮነት እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን መግለጻቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡09:24