Fana: At a Speed of Life!

ኢሬቻን በዩኔስኮ በማስመዝገብ የቱሪስት መስሕብነቱን ማሳደግ ይገባል – የበዓሉ ታዳሚዎች

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 27 ፣2016፣ (ኤፍ ቢ ሲ) የኢሬቻ በዓል ራሱን ችሎ በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) እንዲመዘገብ በማድረግ የቱሪስት መዳረሻነቱን ማሳደግ እንደሚገባ የበዓሉ ታዳሚዎች አመለከቱ፡፡

የሆረ አርሰዴ የኢሬቻ በዓል በቢሾፍቱ ከተማ በተለያዩ ሁነቶች ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ እየተከበረ ነው፡፡

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያነጋገራቸው የበዓሉ ታዳሚዎች፤ ኢሬቻ የምስጋና፣ የእርቅ፣ የሠላም፣ የአንድነት እና የወንድማማችነት በዓል ነው ብለዋል፡፡

የሆረ አርሰዴ የኢሬቻ በዓል ተሳታፊዎችም አባገዳዎች ባስቀመጡት አቅጣጫ መሰረት ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ እያከበሩ መሆኑን አንስተዋል፡፡

የበዓሉ ተሳታፊዎች የተለያዩ ባህላዊ አልባሳትን በመልበስና በዓሉን የሚያንጸባርቁ ባህላዊ ዜማዎችን በመጫወት ለበዓሉ ልዩ ድምቀት እንዳጎናጸፉት ተናግረዋል፡፡

የኢሬቻ አከባበር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየደመቀ መምጣቱን የገለጹት ተሳታፊዎቹ÷ በቀጣይ በዓሉን ራሱን አስችሎ በዩኔስኮ በማስመዝገብ የቱሪስት መስሕብነቱን ማሳደግ ይገባል ብለዋል፡፡

በተለይም የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገራት ጎብኚዎች በበዓሉ እንዲሳተፉ የበዓሉን ባህላዊ እሴት በሚገባ ማስተዋወቅና ማስገንዘብ አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ለዚህም ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በቅንጅትና በትብብር ሊሰሩ እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.