Fana: At a Speed of Life!

የሆራ አርሰዲ የኢሬቻ በዓል በሰላም መከበሩን የጋራ ግብረ-ኃይሉ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሆራ አርሰዲ የኢሬቻ በዓል የገዳ ሥርዓት እሴቶችን በጠበቀ መልኩ በሰላም ተከብሮ መጠናቁን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ-ኃይል አስታወቀ፡፡

አባ ገዳዎች፣ ሀደ ሲንቄዎች፣ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎችና ከጎረቤት ሀገራት የመጡ እንግዶችና ቱሪስቶች የታደሙበት የ2016 ዓ.ም ሆራ አርሰዲ የኢሬቻ በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም መከበሩን ገልጿል፡፡

የቢሾፍቱ ከተማ ነዋሪዎች፣ የበዓሉ አስተባባሪዎችና የአስተዳደር አካላት በዓሉን ለማክበር ወደ ከተማዋ የመጡ እንግዶችን በገዳ ሥርዓት እሴቶች መሠረት በወንድማማችነትና በእህትማማችነት መንፈስ ተቀብሎ በማስተናገድ ካከናወኑት ተግባር ባሻገር ከፀጥታ ኃይሉ ጋር በመቀናጀት ለበዓሉ ሰላማዊነት ከፍተኛ አስተዋፅኦ በማበርከታቸው የሆራ አርሰዲ የኢሬቻ በዓልም ያለምንም የፀጥታ ችግር መከበሩንም ግብረ-ኃይሉ አስታውቋል፡፡

ለበዓሉ በሰላም መከበር የድርሻቸውን ለተወጡ ለመላው የኦሮሞ ህዝብ፣ ለብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች፣ ለቢሾፍቱ ከተማ ነዋሪዎች፣ ለአባ ገዳዎችና ሀደ ሲንቄዎች፣ ለበዓሉ አዘጋጅ ኮሚቴዎችና ለወጣቶች በሙሉ ግብረ-ኃይሉ ምስጋና ማቅረቡን የፌደራል ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡

ለበዓሉ ፍፁም ሰላማዊነት ከዋዜማው ጀምሮ እስከ በዓሉ ማጠናቀቂያ ድረስ ኃላፊነታቸውን በትጋትና ለተወጡ የፀጥታ ተቋማት አመራሮችና አባላትም የጋራ ግብረ-ኃይሉ ምስጋና አቅርቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.