አቶ አህመድ ሺዴ እና አቶ ማሞ ምሕረቱ ከአይ ኤም ኤፍ ዋና ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ ፣ መስከረም 30 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ እና የብሔራዊ ባንክ ገዢ አቶ ማሞ ምሕረቱ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ ኤም ኤፍ) ዋና ዳይሬክተር ክርስታሊና ጆርጂዬቫ ጋር ተወያዩ።
ውይይቱ በሞሮኮ እየተካሄደ ካለው የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም እና የዓለም ባንክ አመታዊ ስብሰባ ጎን ለጎን የተካሄደ መሆኑን የብሄራዊ ባንክ መረጃ ያመላክታል።
በውይይታቸው ወቅትም በኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚክ ማሻሻያ ፕሮግራም ላይ መክረዋል።