Fana: At a Speed of Life!

ሮታሪ አዲስ አበባ ምዕራብ እና የሮታሪ ታይዋን ታይፒ ሲን ዪ 2 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር የሚያወጡ የህክምና ቁሳቁሶች ለገሱ

አዲስ አበባ፣ግንቦት 9፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ)ሮታሪ አዲስ አበባ ምዕራብ እና የሮታሪ ታይዋን ታይፒ ሲን ዪ ለኮቪድ ህክምና ማዕከል 2 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር የሚያወጡ የህክምና ቁሳቁሶች መለገሳቸውን የጤና ሚኒስትር ገለጹ።

የጤና ሚኒስትሯ ዶክትር ሊያ ታደሰ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ እንደገለጹት÷ድጋፉ በሚሌንየም አዳራሽ የተሰራውን የኮቪድ ህክምና ማዕከል ዝግጁነት ለማጎልበት እንዲያግዝ  የሚውል ነው ብለዋል።

ድርጅቶቹ 2 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር የሚገመት ዋጋ የሚያወጡ የህክምና ቁሳቁስ አቅርቦቶች በመለገሳቸውም ዶክተር ሊያ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.