Fana: At a Speed of Life!

በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ የተመረቁት የኢነርጂ ፋብሪካዎች …

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለኢነርጂ ዘርፉ ተደማሪ አቅም የሚሆኑ ፋብሪካዎችን በሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ መርቀው ከፍተዋል፡፡

በዛሬው እለት ከተመረቁት ፋብሪካዎች መካከል አንዱ የቶዮ ሶላር ኢነርጂ ሁለተኛው ምዕራፍ ነው፡፡ ኩባንያው በ170 ሚሊየን ዶላር ኢንቨስትመንት የተቋቋመ ሲሆን፤ 1 ሺህ 600 ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል ፈጥሯል፡፡

እጅግ ዘመናዊ ሆኖ የተገነባው ፋብሪካው ዓመታዊ የማምረት አቅሙ 4 ጊጋ ዋት ሀይል ነው፡፡

ሁለተኛው ፋብሪካ ደግሞ በሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ማዕዘን ላይ የሚገኘው ኦሪጅን ሶላር ሲሆን፤ በ55 ሚሊየን ዶላር ኢንቨስትመንት ተገንብቶ ስራ ጀምሯል፡፡

ከ90 በመቶ በላይ ዘመናዊ የአውቶሜሽን ስራ የተገጠመለት ኩባንያው በዓመት 4 ነጥብ 3 ጊጋ ዋት ሀይል ያመነጫል፡፡

ሶስተኛው የዘርፉ ተዋናይ ሉሚንቴክ ሶላር በ100 ሚሊየን ዶላር ኢንቨስትመንት ተጀምሮ 1 ሺህ 500 የስራ እድሎች የፈጠረ ሲሆን፤ በዓመት 3 ጊጋ ዋት ሀይል ያመነጫል፡፡

በአጠቃላይ ሶስቱ የሶላር ፋብሪካዎች ከ11 ነጥብ 3 ጊጋ ዋት ንፁህ ኃይል የሚያመነጩ ተደማሪ አቅሞች ሲሆኑ፤ ፋብሪካዎቹ ከሀገር ውስጥ የኃይል ፍጆታ በተጨማሪ ለውጭ ገበያ በማቅረብ ለውጭ ምንዛሪ ግኝት ቁልፍ ሚና ይጫወታሉ፡፡

እነዚህ ቁልፍ ኩባንያዎችን የሚደግፈው የኤች.ዜድ ጋዝ ፋብሪካ በዛሬው እለት የተመረቀ አራተኛው ፋብሪካ ነው፡፡

ለሶላር ኢንዱትሪውን የጀርባ አጥንት በመሆን የሚደግፈው ፋብሪካው ለሶስቱ የሶላር ፋብሪካዎች የሚያስፈልጉ መሰረታዊ ጋዞችን በማምረት የሚያቀርብ ፋብሪካ ነው፡፡

በ6 ሚሊየን ዶላር ካፒታል የተገነባው ፋብሪካው ከ100 በላይ ሰራተኞች ያሉት ሲሆን፤ በዓመት 900 ቶን ኦክስጅን፣ 40 ሺህ ቶን ናይትሮጅን እና 7 ቶን ሃይድሮጅን የማቅረብ አቅም አለው፡፡

በሚኪያስ አየለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.