Fana: At a Speed of Life!

የብልፅግና ፓርቲ ኦሮሚያ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት በአርቲስት ሀሎ ዳዌ ህልፈት የተሰማውን ሃዘን ገለፀ

 

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልፅግና ፓርቲ ኦሮሚያ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማ በአርቲስት ሀሎ ዳዌ ህልፈት የተሰማቸውን ሃዘን ገለፁ፡፡

አርቲስት ሀሎ ከአፍራን ቀሎ የሙዚቃ ኮከቦች ጋር በመሆን የኦሮሞን ህዝብ ኪነጥበብ በማሳደግና ለህዝብ ድምፅ የሆነች ብርቱ ሰው ነበረች ነው ያሉት አቶ ፍቃዱ ተሰማ በሃዘን መግለጫቸው፡፡

“አርቲስት ሀሎ ዳዌ ሙዚቀኛ ብቻ ሳትሆን በሀገራችን ነፃነትና እኩልነት ተረጋግጦ የሀገራችን ህዝቦች በእኩልነትና በወንድማማችነት እንዲኖር በሙዚቃ ስራዎቿ ትልቅና የማይረሳ ስራ የሰራች ታጋይም ጭምር ናት” ብለዋል።

ሀሎ ዳዌ ለህዝባችን የሙዝቃ እድገትና ለነፃነት ትግል ያበረከተችው አስተዋፅኦ በዘመን የሚወሰን ሳይሆን ለዘመናት ከኛ ጋር የሚኖር አሻራ ነው ሲሉም ገልጸዋል።

ተሰምተው በማይጠገቡ ስሜት ቀስቃሽ በሆኑ የሙዚቃ ስራዎቿ የተወችልን የኪነጥብ ሥራ ትውልድ እንደ መስታዎት ራሱን የሚመለከትበት፣ የሚማርበትና ለቀጣይ ትውልድ የሚተላለፍ ነው ብለዋል።

ለኦሮሞ ህዝብ እንደ ሀሎ ዳዌን የመሰለች ጠንካራ አርቲስትና ተጋይ ማጣት መሪር ሀዘን ቢሆንም ትውልድ ከዘመን አይሽሬው ስራዎቿ እየተማረ የተሻለ ስራዎችን በመስራት ሲዘክራት ይኖራል ነው ያሉት አቶ ፍቃዱ።

ለቤተሰቦቿ፣ ለዘመዶቿ እንዲሁም ለስራዎቿ አድናቂዎችና ለኦሮሞ ህዝብ መፅናናትን ተመኝተዋል፡፡

አርቲስት ሐሎ ዳዌ ባደረባት ሕመም በህክምና ስትረዳ ቆይታ በትናንትናው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.