Fana: At a Speed of Life!

በተለያዩ ማዕከላት የሚገኙ ሠልጣኞች የልማት ሥራዎችን ጎበኙ

 

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ “ዕዳ ወደ ምንዳ” በሚል መሪ ሐሳብ በአዲስ አበባ፣ አርባ ምንጭ ፣ጅግጅጋ እና ጅማ ማዕከላት እየተሰጠ በሚገኘው 2ኛው ዙር ሀገር አቀፍ ስልጠና እየተሳተፉ የሚገኙ የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች የልማት ሥራዎችን ጎበኙ፡፡

በአዲስ አበባ ማዕከል ስልጠናቸውን እየተከታተሉ የሚገኙ አመራሮች የከተማዋን ግዙፍና ሰው ተኮር ፕሮጀክቶች በዘጋቢ ፊልም የተመለከቱ ሲሆን አንዳንዶችንም በአካል በመጎብኘት ልምድ እንዲቀስሙ እየተደረገ ነው።

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ስልጠናው ጠንካራ ፓርቲ በመገንባት መንግስትን ለማጠናከር በጊዜ ቀመር የተቀመጡ የፓርቲያችንን ራዕይዎች ለማሳካት እርስ በእርስ መማማርን ዓላማው አድርጎ እየተካሄደ መሆኑን አስገንዝበዋል።

በተመሳሳይ በአርባ ምንጭ ማዕከል ያሉ ሰልጣኞች÷ በጋሞ ልማት ማህበር የአርባምንጭ ግብርና ልማት እንቅስቃሴን ጎብኝተዋል፡፡

እንዲሁም የጅግጅጋ የስልጠና ማዕከል ስልጠኞች በሶማሌ ክልል ፋፈን ዞን በሸበሌ የሚገኝ ዘመናዊ የግመል እርባታ ካምፕን ፣ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ የሚገኘው ዶሮ እርባታ ፣ የቱሉ ጉሌድ እርሻ ፣ የፋፈን የእርሻ ማሳ እና የተሰሩ የውሃ መሠረተ ልማት ጎብኝተዋል፡፡

በተመሳሳይ በጅማ ማእከል ስልጠናቸውን እየተከታተሉ የሚገኙ የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች በጅማ ዞን ሸቤ ሰንቦ ወረዳ የሩዝ ክላስተርን ጎብኝተዋል።
በመስክ ጉብኝቱ ከሩዝ ክላስተር በተጨማሪ በሰቃ ጨቆርሳ ወረዳ የተለያዩ የልማት ስራዎች ተጎብኝቷል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.