የአርቲስት ሐሎ ዳዌ ቀብር ሥነ-ሥርዓት ተፈፀመ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአርቲስት ሐሎ ዳዌ ቀብር ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ከተማ ተፈፀመ፡፡
በቀብር ሥነ -ሥርዓቱ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች፣ የአርቲስቷ ቤተሰቦች፣ የሙያ አጋሮች እና አድናቂዎች ተገኝተዋል፡፡
ለኦሮሞ ኪነ-ጥበብ እድገት አስተዋጽኦ ካበረከቱ ታዋቂ አርቲስቶች አንዷ የሆነችው አርቲስት ሐሎ ዳዌ ባደረባት ሕመም ለረጅም ጊዜ ሕክምና ስትከታተል ቆይታ ጥቅምት 3 ቀን 2016 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት መለየቷ ይታወሳል።