Fana: At a Speed of Life!

አቶ ሙስጠፌ መሀመድ የክልሉ ተወላጅ ዳያስፖራዎች በልማት ስራ ላይ የሚያደርጉትን ተሳትፎ እንዲያጠናክሩ ጠየቁ

 

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ የክልሉ ተወላጅ ዳያስፖራዎች በክልሉ በልማት ስራ ላይ የሚያደርጉትን ተሳትፎ እንዲያጠናክሩ ጥሪ አቀረቡ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በጅግጅጋ ከተማ ታይዋን ማዕከል በደረሠው የእሳት አደጋ ተጎጂዎችን ለመደገፍ ከኖርዌይ እና ሰሜን አሜሪካ ከመጡ የክልሉ ተወላጅ ዳያስፖራዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱ ላይ ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ ÷ የክልሉ ተወላጅ ዳያስፖራዎች በገበያ ማዕከሉ ቃጠሎ የተጎዱ ነጋዴዎችን ለማቋቋም ላደረጉት የገንዘብ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ድጋፉ የክልሉ ዳያስፖራዎች በክልሉ ልማት ላይ ለሌሎች ምሳሌ የሆነ ስራ እያከናወኑ እንደሚገኙ የሚያሳይ ተግባር ነው ብለዋል።

ርእሰ መስተዳድሩ የክልሉ ተወላጅ ዳያስፖራዎች በቀጣይም በክልሉ ልማት ላይ የሚያደርጉትን ተሳትፎና አስተዋፅኦ አጠናክረው እንዲያስቀጥሉ ጥሪ ማቅረባቸውን የሶማሌ ክልል መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.