የጋራ መግባባት በመፍጠር ሀገርንና ህዝብን ለማሻገር እየተሰራ ነው – አቶ አደም ፋራህ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለአመራሩ ቀጣይ ተልዕኮ ወሳኝ በሆኑ መሠረታዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት በመፍጠር ሀገርን እና ህዝብን ለማሻገር እየተሰራ ነው ሲሉ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ ተናገሩ፡፡
አቶ አደም ፋራህ ከ”ዕዳ ወደ ምንዳ” በሚል መሪ ሀሳብ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሆሳዕና ማዕከል ስልጠና እየተከታተሉ ለሚገኙ ከመላዉ ኢትዮጵያ ለተውጣጡ አመራር ሠልጣኞች መልዕክት አስተላልፈዋል።
አቶ አደም እንደገለጹት÷ ለአመራሩ ቀጣይ ተልዕኮ ወሳኝ በሆኑ መሠረታዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት በመፍጠር ሀገርን እና ህዝብን ለማሻገር እየተሰራ ነው።
ያሉንን እድሎች በተገቢው መንገድ በመጠቀም ለሀገር እና ለህዝብ ጥቅም በጋራ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል ምክትል ፕሬዚዳንቱ።
የብልጽግና ፓርቲ ሀገር መምራት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊው፣ በፖለቲካው ዘርፍ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማሳደግ ያስቻለ መሆኑን መናገራቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ስልጠናው በአመራሩ መካከል የጋራ አንድነት ፈጥሮ ለህዝብ የገባነውን ቃል በአግባቡ ለመፈጸም እና ከህዝብ የተቀበልነውን አደራ በውጤታማነት እንድንወጣ የሚያስችል ነው ብለዋል።
አቶ አደም በሆሳዕና ከተማ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤትን መጎብኘታቸው ተገልጿል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!