Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ብርሃኑ ከጅቡቲ የዓለም አቀፍ ፍልሰተኞች ድርጅት ኃላፊ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጂቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ ከጅቡቲ የዓለም አቀፍ ፍልሰተኞች ድርጅት ኃላፊ ታንጆ ፓስፊኮ ጋር ተወያዩ፡፡

በውይይታቸውም በጅቡቲ እየተባባሰ የመጣውን ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ለመከላከል ሁለቱ ሀገራት በጋራ ሊሰሩባቸው በሚገቡ ጉዳዮች ላይ ምክክር አድርገዋል፡፡

በተጨማሪም በፍልሰተኞች መጠለያ ስፍራዎች የዜጎችን ደህንነት ለመጠበቅ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ማሻሻል በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያም መክረዋል፡፡

ሁለቱ ወገኖች የስደትን አስከፊነት ለህብረተሰቡ ማስገንዝብ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ መድረሳቸውን በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.