Fana: At a Speed of Life!

3ኛው ዙር የህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር በካይሮ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 3ኛው ዙር የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት እና አለቃቀቅ ደንቦችና መመሪያዎች የሶስትዮሽ ድርድር በግብጽ ካይሮ መካሄድ ጀምሯል፡፡

በድርድሩም ባልተፈቱ የቴክኒካል እና የህግ ማእቀፍ ጉዳዮች የተሻለ ውጤት ላይ ለመድረስ ትኩረት እንደሚደረግ የኢትዮጵያ ወገን ተደራዳሪዎች ልዑካን መሪ አምባሳደር ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

ኢትዮጵያ በ2015 በመሪዎች ደረጃ የተፈረመው የመርሆች መግለጫ ስምምነት መሰረት ድርድሩን በፍትሃዊና ምክንያታዊ አጠቃቀም መርህ መሰረት ውጤት ላይ ለመድረስ እንደምትሰራም ተጠቁሟል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.