Fana: At a Speed of Life!

አቶ አሻድሊ በአብራሞ ወረዳ በመኸር እርሻ የለማን የስንዴ ማሳ ጎበኙ

 

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ርዕሰ-መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን የተመራ ልዑክ በአብራሞ ወረዳ በመኸር እርሻ የለማን የስንዴ ማሳ ጎብኝቷል፡፡

ርዕሰ-መስተዳድሩ በጉብኝቱ ወቅት እንዳሉት÷ በአብራሞ ወረዳ የለማው የስንዴ ሰብል በጥሩ ሁኔታ ላይ መገኘት ከአርሶ አደሩ እስከ ከፍተኛ አመራሩ ለስንዴ ልማት ስራው ያደረጉት ርብርብ ውጤት ማሳያ ነው፡፡

በሚቀጥሉት ዓመታት በክልሉ የስንዴ ምርታማነትን በማሳደግ ለገበያ ከማቅረብ ባለፈ ፋብሪካዎችን ለመመገብ ግብ ተይዞ እየተሰራ እንደሚገኝም ርዕሰመስተዳድሩ አስታውቀዋል፡፡

የአብራሞ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አታላይ ደረጀ ÷በወረዳው በመኸር ስንዴ 1ሺ 600 ሄክታር መሬት በዘር መሸፈኑን ገልጸው በወረዳው 33 ቀበሌዎች የመኸር ስንዴን በክላስተር እያለሙ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡

በተያዘው የመኸር እርሻም 125ሺህ ኩንታል ምርት እንደሚጠበቅ መናገራቸውን ከክልሉ ሚዲያ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.