Fana: At a Speed of Life!

116ኛውን የሠራዊት ቀን አስመልክቶ የፎቶ አውደ ርዕይ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 116ኛውን የመከላከያ ሠራዊት ቀን አስመልክቶ የፎቶ አውደ ርዕይ በብሔራዊ ቴአትር ተካሂዷል።

አውደ ርዕዩ ፥ የጥንት አባቶችን ማንነት መሰረት ያደረገ የቅድመ ዘመናዊ ኢትዮጵያ አመሰራረትና እድገት ከ1900 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 2016 ዓ.ም በተለያዩ ጊዜ መከላከያን ሲመሩ የነበሩ ሚኒስትሮችና ኤታማዦር ሹሞችን ታሪክ የሚገልጹ መረጃዎች በጽሑፍና በፎቶ ተሰንደው ለእይታ በቅተዋል።

ዓርበኞች፣ የቀድሞ የሠራዊት አባላት እና አመራሮች፣ የሠራዊቱ ከፍተኛ አመራሮችና አባላቱ የፎቶ አውደ ርዕዩን ጎብኝተዋል።

ኢትዮጵያን ለማቆየት የጥንት አባቶቻችን የእውቀት፣ የደም፣ የአጥንትና የህይወት ዋጋ በመክፈል ዛሬ ላለንበት ደረጃ አብቅተውናል ያሉት ኤግዝብሽኑን የከፈቱት ጀኔራል ጌታቸው ጉዲና ናቸው፡፡

አሁን ያለው ትውልድም የበፊቱን ታሪክ በማስቀጠል የተሰነዱ ቅርስና ታሪኮቻችንን በመጠበቅ ለመጪው ትውልድ ማስተላለፍ ይገባዋል ብለዋል፡፡

የመከላከያ ሚኒስቴር ልዩ ስታፎች ጉዳይ ዘርፍ ኃላፊ ሜጄር ጄኔራል ጥሩዬ አሰፌ ፥ የፎቶ ኤግዚቢሽኑ የሠራዊት አመሰራረት ታሪኮቻችንን ወደኃላ መለስ ብሎ የሚያስቃኝ ነው ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ ታሪክም የሠራዊታችን ጀግንነት ከጥንት ዓርበኞች አባቶቻችንና እናቶቻችን የመጣ መሆኑን የሚያሳይ እንደሆነና አሁን ላለንበት ደረጃ ለሠራዊታቸን ግንባታ ትልቅ አንድምታ እንዳለው ተናግረዋል፡፡

ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል የተሰነደውን ታሪክ አውቆ ሊማርበት እንደሚገባ ማሳሰባቸውን የመከላከያ ሠራዊት መረጃ ያመለክታል።

የፎቶ አውደ ርዕዩ እስከ ፊታችን ጥቅምት 17 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ለጎብኚዎች ክፍት እንደሚሆን ተጠቁሟል፡፡
#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.